Welcome to Ethio One
You may explore the site and learn more about our services. If you are a new user, you may register to access our services.
ኢትዮ ዋን ቀላል እና ፈጣን አስተማማኝ የቢዝነስ ስኬት አጋርዎ!
Welcome to Ethio One
You may explore the site and learn more about our services. If you are a new user, you may register to access our services.
ስለ ኢትዮ ዋን
Ethio One
ኢትዮ ዋን በግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም. (May 12, 2023) በኩሩ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የተቋቋመ የኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (ኃ/የተ/የግ/ማ) ነው። ድርጅቱ ትኩረቱን በአገልግሎት ዘርፍ ላይ በማድረግ፣ ሀገር በቀል የቁጠባና የኢንቨስትመንት ሥርዓቶችን በማዘመን ላይ ይሰራል—ለአብነት ያህል፣ ባህላዊ እቁብን በኢ-ኮመርስ (በቴክኖሎጂ) በማዘመን እንዲሁም የሥራ ፈጠራና የግል ብቃት ማሳደጊያ ሥልጠናዎችን በመስጠት ላይ ያተኩራል።
የኢትዮ ዋን ዋና መሥሪያ ቤት በኢትዮጵያ የሚገኝ ሲሆን፣ በተለያዩ ከተሞችም የቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶችን ለመክፈት በሒደት ላይ ይገኛል።
የኢትዮ ዋን መሥራቾች በጋራና በኅብረት መሥራት ያመኑ፣ በንግድና በሥራ ፈጠራ ዘርፍ በቂ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች ናቸው።
ኢትዮ ዋን ከደንበኞች፣ ከድርጅቱ ሠራተኞች እና ከቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች—በአጠቃላይ ከማንኛውም የማኅበረሰብ አካል ጋር በቅንጅት በመሥራት የግለሰቦችንና የሀገርን ኢኮኖሚ የመገንባት ራዕይ ሰንቆ የሚሠራ የንግድ ድርጅት ነው።
ራዕይ
ለደንበኞቻችን የላቀ አገልግሎት በመስጠት እና ጠንካራ እምነትን በመገንባት፣ በአገልግሎት ዘርፍ ግንባር ቀደም መሆን።
ተልዕኮ
ራዕያችንን ለማሳካት የጋራ ሀሳቦችን ባለቤትነት በመውሰድ፣ በማሻሻል፣ በመማማር እና እርስ በእርስ በመደጋገፍ ጠንካራ እና ዘላቂ ኢኮኖሚ መገንባት።
መመሪያ
ምርታማነትን ማሳደግ እና አዳዲስ ፈጠራዎችን ተግባራዊ ማድረግ።
የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
የኢትዮ ዋን የቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ህብረት ስራ ማህበር አገልግሎቶች
ዋና ዋና የቁጠባ አገልግሎቶች:-
- መደበኛ ቁጠባ (Compulsory Saving)
- የፈቃደኝነት ቁጠባ (Voluntary Saving)
- የጊዜ ገደብ ቁጠባ (Time Deposit Saving)
- የንግድ / የቀን ገቢ ቁጠባ (Trade / Daily Income Saving)
- የቤት ቁጠባ (Housing Saving)
- የመኪና ቁጠባ (Car Saving)
- የሴቶች ልዩ ቁጠባ (Women's Special Saving)
- የወጣቶች / ተማሪዎች ቁጠባ (Youth / Student Saving)
- የህፃናት / ልጆች ቁጠባ (Children Saving)
- የድርጅት ቁጠባ (Institutional Saving)
አገልግሎቶቻችን
- የግል እድገት እና የንግድ ሥልጠናዎች
- ዘመናዊ የዕቁብ አገልግሎት
- ቁጠባ እና ብድር
- የዲጂታል ንግድ (eCommerce) እና የሥራ ዕድል ፈጠራ
- የገቢና ወጪ ንግድ (Import-Export)
የኢትዮ ዋን መደበኛ ተግባራት
- የአገልግሎት ማብራሪያና የኃላፊነት ክፍፍል፡ ለአባላትና ደንበኞቻችን ስላሏቸው አገልግሎቶች ግልጽ ማብራሪያ መስጠት እንዲሁም የጋራ ኃላፊነትን በመጋራት አብሮ መስራት።
- የትብብር ስራና ተሞክሮ ልውውጥ፡ ከአንጋፋና ልምድ ካላቸው አመራሮች ጋር በቅንጅት መስራት እና የእውቀትና ልምድ ልውውጥ ማድረግ።
- የተቋም ማስተዋወቅና ስልጠና፡ ተቋሙን በስፋት ማስተዋወቅ፣ እንዲሁም አቅምን የሚገነቡ መደበኛ ስልጠናዎችን ማደራጀትና መስጠት።
- የማበረታቻ ስጦታዎችና ማስተዋወቂያዎች፡ ለደንበኞቻችን ልዩ ልዩ የማበረታቻ ስጦታዎችን፣ ጥቅማጥቅሞችንና ማስተዋወቂያዎችን (Promotions) ማቅረብ።
ኢትዮ ዋን ፐሮሞሽን እና ኢቨንት የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
- አምራችና ተጠቃሚን ማገናኘት
- ምርትና አገልግሎትን ማስተዋወቅ
- ግዢወችን በቀጥታ ለተጠቃሚው ማድረስ
- ትላልቅ ባዛሮችን በምቹ ቦታ ላይ ማዘጋጀት
- የግብይት ሰንሰለቶችን መዘርጋት